እምነታችን
ሁሉን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን ፣ ዓለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ አንድ የአብ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚስተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ በሰማይም ካለው በምድርም ካለው ያለርሱ ምንም ምን የሆነ የለም። ስለኛ ስለሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ፣ ደግሞ ስለኛ ተሰቀለ። በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ፤ ሞተ፣ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተሰሣ ፤ በቅዱሳት መጻህፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደሰማይ ዐረገ ፣ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፣ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም። በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱ ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብና ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን ፣ እናመሰግነዋለን ፤ እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነው። ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ክብርት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን፤ የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ።